Jonny Ragga - Atifred (Wiha)
ጆኒ ራጋ - አትፍረድ (ውሃ)
Track 1 of 8 from the album Jonny Ragga - Wiha Ena Esat | Wiha
Lyrics: Jonny Ragga
Melody: Jonny Ragga
Arrangement: Jonny Ragga
Producer: Jonny Ragga
Mixing: Nicolas SÉLAMBIN at 129H STUDIO (FRANCE)
Mastering: Sébastien «Mellow Mood » Houot at Wise Studio (FRANCE)
© 2025 All Rights Reserved
Produced by Jonny Ragga for Terara Music Production.
Any unauthorized use, copying, or distribution is strictly prohibited.
_________________________________
ኦሆሆሆ ኤሄሄሄ ላላላላላላ
እውነትን ተዛመድ
ከሌላው ህይወት ውረድ
እስክታውቅ ድረስ አታውቅም
በሰው ላይ አትፍረድ
ምናልባት ሞልቶ ብታየው ፈገግታዬን ከፊቴ
አይምሰልህ በድሎት የተሞላ ህይወቴ
ብታየኝ ዘንጬ ፋሽኑንም ለብሼ
የትናንትናው ሽንፈቴ ላይ በፅናት ታድሼ
ካላየህ ሆነህ በኔ ቦታ
ላትረዳው የኔን እውነታ
ሩቅ ሆኖ
ከቶ አይገባህም የኔ ምልከታ
ካላየህ ገብተህ በኔ ጫማ
አለሜን ማውቅ ካልቻልክማ
በማዶ ሆኖ
በመላምትህ አልስማማም
ደሞ እንደ ጉም ባዶ
እንደ ህልም ከእውነታው ማዶ
ብቻ አይቶ መልኩን ሳያውቅ ታሪኩን
ይሰፍራል ልኩን
ደሞ እንደ ጉም ባዶ
እንደ ህልም ከእውነታው ማዶ
ሳያውቅ እርግጡን ሳይረዳ ጭብጡን
ይሸ - ይሸጣል ሸፍጡን
ስታውቀኝ ታውቀኛለህ
ግን እስከዛው ሐሜቱ የሞተ ለዛው
በሬ ወለደ ወሬ ማነው ሚነዛው
ስታውቀኝ ትፈርዳለህ
ሀቅ የለም ደብዛው ውሸት መርዛው
ወፍ ዘራሽ ወሬ ነው ጆሮ የሚገዛው
ስታውቀኝ ታውቀኛለህ
ግን እስከዛው ሐሜቱ የሞተ ለዛው
በሬ ወለደ ወሬ ማነው ሚነዛው
ስታውቀኝ ትፈርዳለህ
ሀቅ የለም ደብዛው ውሸት መርዛው
ወፍ ዘራሽ ወሬ ነው ጆሮ የሚገዛው
ታሪኩ ይቀጥላል
ልብ ያለው ልብ ይበል
ጆሮ ያለው ይስማ
የሰው ልጅ ዘንግቶ በአይኑ ያለውን ምሰሶ
የሌላውን ጉድፍ ለማውጣት ይሞክራል ደርሶ
ተዘፍቆ በራሱ ህይወት በሞላበት እንከን
አይሰንፍም ለመፍረድ ሌላ ሰው ጊዜ ማባከን
አይ ሰው አይ ሰው
በሰፈረበት መስፈሪያ እሱም ተራው እስኪደርስ አይቀር መሰፈሩ
ከላይ ብቻ ነው ፍርዱ ለሁሉም ይደርሳል እንደስራ ግብሩ
ሳይሰየም ዳኛ፣ ያው ተጎጂው ተመርጦ የአቦሰጥ ተረኛ
ተከሳሽ ቀርቦ እሱን ሳይረዳ
ከሳሽ በሌለበት ሸንጎ ውሎ ጓዳ
አውታረ መረብ ሐሜቱን ወጥሮ
አይኑን በጨው አጥቦ
አዲስ ወሬ ፈጥሮ ቆርጦ ቀጥሎ
ለይቶ በጎ ነጥሎ ክፋት ላይ ብቻ አነጣጥሮ
በአንዱ ግለሰብ ህይወት እሳቱን ለኩሶ
የተከበረ አርክሶ
ስራ አክስሮ ደርሶ ጥላቻ ተንኩሶ
ታሪክ በጭቃ ለውሶ
ቤተሰብ አፍርሶ
አቤት የወሬ አዋጅ የሞላበት አለም
ሚሉት የልብ ወዳጅ እረ ፍፁም የለም
የተውሶ ማንነት የቆሸሸ ሰልቫጅ
ምላስ ሀቅን ትታ በሀሰት የምትዋዥ
ስሜ መነሳቱ ቢሆን እንኳን ግዳጅ
መክሰሱ መብትህ ነው ግን ፍርዱን ተው ለፈራጅ
ስታውቀኝ ታውቀኛለህ
ግን እስከዛው ሐሜቱ የሞተ ለዛው
በሬ ወለደ ወሬ ማነው ሚነዛው
ስታውቀኝ ትፈርዳለህ
ሀቅ የለም ደብዛው ውሸት መርዛው
ወፍ ዘራሽ ወሬ ነው ጆሮ የሚገዛው
ስታውቀኝ ታውቀኛለህ
ግን እስከዛው ሐሜቱ የሞተ ለዛው
በሬ ወለደ ወሬ ማነው ሚነዛው
ስታውቀኝ ትፈርዳለህ
ሀቅ የለም ደብዛው ውሸት መርዛው
ወፍ ዘራሽ ወሬ ነው ጆሮ የሚገዛው
- Category
- music